የአማርኛ ቃላት ብዛት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሊደር እንደሚችል አረጋግጫለሁኝ
የአማርኛ ቃላት ብዛት እስከ ሦስት ሚሊዮን ሊደር እንደሚችል ያረጋገጥኩት፤ የመጀመሪያ አንድ ሚሊዮን ቃላት አምስት አመት ፈጅቶብኝ ከሰበሰብኩኝ በኋላ ነው። ይህ ሙከራዬ እጅግ አድካሚ ቢሆንም እስከ ዛሬ በአማርኛ ቃላት ላይ ተሰሩ የሚባሉ ስራዎችን ሁሉ ሊወዳደር አሊያም ሊበልጥ እንደሚችል አምኜበታለሁ። በእርግጥ ልፋቱ በገንዘብ ለመተመን እጅግ ያዳግተኛል። ቃላቶችን ለመሰብሰብ የተጠቀምኩባቸው ቴክኖሎጂዎች ከፍተኛ አቅም ያላቸው ኮምፑተሮች የሚፈልግ ስለ ነበር፤ ሥራዬን ፈታኝ አድርጎብኛል። የአማርኛ ቃላት ብዛት ከሦስት ሚሊዮን በላይ መሆናቸውን የተሻለ ማረጋገጫ ያለው፤ አሊያም ቀሪዎቹን ሁለት ሚሊዮን የሚደርሱ ቃላት አብሮ ለመሰብሰብ የበጀት እና የቴክኖሎጂ አቅሙ ያለው ቢገኝ ጥሩ ነበር። የቃላት ግድፈት ችግር ለምሳሌ ብንወስድ በመጻሕፍት፣ በጋዜጦችና በመጽሔቶች ላይ ሆነ በተለያዩ የማስታወቂያ ጽሑፎች ላይ በብዛት የሚታይ ብቻ ሳይሆን ከእንግሊዝኛ ጽሑፍ ጋር ሲነፃፀር በአማርኛው ላይ የሚታዩት ስህተቶች (ግድፈቶች) እጅግ የበዙ ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ አንደኛው ምክንያት የምንገለገልባቸው የአማርኛ መጻፊያ ሶፍትዌሮች የቃላት ማረሚያ ስለሌላቸው ነው፡፡ ስለሆነም የቃላት ማረሚያ ያለው የአማርኛ መጻፊያ ሶፍትዌር ቢሰራ ለጽሑፍ ስራዎቻችን ጥራት መሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ባለሙያዎቹ ይናገራሉ፡፡ ለሁሉም ግን ቃላቶቹ መሰብሰብ ቀዳሚ ነው። የነገሩ አሳሳቢነት ብዙ ቦታዎች የተዘገብ ጉዳይ ነው። ሀይሉ ወርቁ አስተያየታችሁን