የፓቶጵያ ፍቅር - ፓቶጵያ የሰው ልጆች ብቸኛዋ ተስፋ
ክፍል አንድ - ዳይስቶጵያ ምዕራፍ - 1. ዮናታን እውነት ባይሆንም ቅሉ መኖር ጣዕም አጥቶ ፣ አለመኖር የሚመረጠው ፤ በንሮ የጎደለው ነገር የነፍስ ጥያቄ ከሆነ ነው ይባላል። ይህ ግን ለሁሉም ሰው አይደለም፤ ለአንዳንዶች እውነት ነው። አንዳንዱ ከበላና ከጠጣ ሌላው ጉዳዩ አይደለም። ሌላው ደግም መኖር የሚባለው ያሻህን ፈልገህ ስታገኝ እና ሲተርፍህ ነው ይላል። ለዮናታን ደሞዝ ግን ንሮ ያም አይደለም። ዮናታን እንደሚለው መኖር ማለት ግዜና ገንዘብ ኖሮህ ፤ ሌሎች ኑሮን ራሱን ሲኖሩት ፤ ምንም ሳይጎልብህ ቆም ብሎ ማየት ሲቻል ነው። ዮናታን እንኳንስ የሌሎች የራሱን እንኳን ቆሞ ማየትን ሳይችል በሚኖርባት አሜሪካ ፤ በኮምፕዩተር ጥገናና የኔትወርክ ደህንነት ባለሙያነት ተቀጥሮ ነው የሚተዳደረው። ከዚህ ሥራው እሱ ንሮ የሚለውን ዓይነት ንሮ ለመኖር የሚያስችል በቂ ግዜና ገንዘብ አያገኝም። በዚያ ላይ እናቱንና ወንድሙን መጦር ተጨምሮበት። የተቀጠረበት ድርጅት ሳይበር ሳን ይባላል ፤ የተሰማራው ፕራይቬት ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት ነው። ሳይበር ሳን የሚገኘው በጆርጂያ ግዛት፣ በአትላንታ ከተማ፣ በሚድታውን ከፍለ ከታማ ነው። ሁሌም እንደሚያደርገው ፣ ዛሬም በዕለተ ሐሙስ “ወይ ንሮ … ” የሚለውን የአስቴር ዘፈን እየኮመኮመ ፤ መኪናውን እያበረረ ከሚሰራበት ድርጅት ወደ ቤቱ ይከንፋል። ምን እንደሚያስከንፈው ባያውቀውም ልቡ ዝም ብሎ ይሮጣል። ሥራ ቦታ ሲሆን ወደ ቤት መሄድ ይፈልጋል