የፓቶጵያ ፍቅር - ፓቶጵያ የሰው ልጆች ብቸኛዋ ተስፋ
ምዕራፍ - 1. ዮናታን
እውነት ባይሆንም ቅሉ መኖር ጣዕም አጥቶ ፣ አለመኖር የሚመረጠው ፤ በንሮ የጎደለው ነገር የነፍስ ጥያቄ ከሆነ ነው ይባላል። ይህ ግን ለሁሉም ሰው አይደለም፤ ለአንዳንዶች እውነት ነው። አንዳንዱ ከበላና ከጠጣ ሌላው ጉዳዩ አይደለም። ሌላው ደግም መኖር የሚባለው ያሻህን ፈልገህ ስታገኝ እና ሲተርፍህ ነው ይላል። ለዮናታን ደሞዝ ግን ንሮ ያም አይደለም። ዮናታን እንደሚለው መኖር ማለት ግዜና ገንዘብ ኖሮህ ፤ ሌሎች ኑሮን ራሱን ሲኖሩት ፤ ምንም ሳይጎልብህ ቆም ብሎ ማየት ሲቻል ነው። ዮናታን እንኳንስ የሌሎች የራሱን እንኳን ቆሞ ማየትን ሳይችል በሚኖርባት አሜሪካ ፤ በኮምፕዩተር ጥገናና የኔትወርክ ደህንነት ባለሙያነት ተቀጥሮ ነው የሚተዳደረው። ከዚህ ሥራው እሱ ንሮ የሚለውን ዓይነት ንሮ ለመኖር የሚያስችል በቂ ግዜና ገንዘብ አያገኝም። በዚያ ላይ እናቱንና ወንድሙን መጦር ተጨምሮበት። የተቀጠረበት ድርጅት ሳይበር ሳን ይባላል ፤ የተሰማራው ፕራይቬት ፕሮፐርቲ ማኔጅመንት ነው። ሳይበር ሳን የሚገኘው በጆርጂያ ግዛት፣ በአትላንታ ከተማ፣ በሚድታውን ከፍለ ከታማ ነው።
ሁሌም እንደሚያደርገው ፣ ዛሬም በዕለተ ሐሙስ “ወይ ንሮ…” የሚለውን የአስቴር ዘፈን እየኮመኮመ ፤ መኪናውን እያበረረ ከሚሰራበት ድርጅት ወደ ቤቱ ይከንፋል። ምን እንደሚያስከንፈው ባያውቀውም ልቡ ዝም ብሎ ይሮጣል። ሥራ ቦታ ሲሆን ወደ ቤት መሄድ ይፈልጋል፤ ቤት ሲሆን ደግሞ የሚሰራው ያጣና ትካዜ ይወረዋል። አንዳንዴ ብቸኝነቱ እንደዚህ እንደሚያደርገው ያስብና ሐበሻ ወደሚበዛባቸው መዝናኛ ቦታዎች ጎራ ይላል። ምን ያደርጋል ፤ እዛም ሲሄድ የሚያዝናናው ነገር ብዙም አያገኝም። ይህንን ሁኔታው ያዩ አንዳንድ ሰዎች ዮናታን አንዳች የጤና እክል ይኖርበት ይሆን ሲሉ ይጠራጠራሉ።
የአስቴር ሙዚቃዎችን እየኮመኮመ ለአንድ ሰዓት የሚሆን ነድቶ በዲካልብ ካውንቲ ውስጥ ፣ ዲክተረ በተባለች ከተማ ወደሚገኘው ቤቱ ደረሰ። ዲክተር ሠላሳ ሺህ የማይበልጥ ነዋሪ ያላት አነስተኛ ከታማ ነች። በሩን ከፍቶ እንደገባ ቴሌቭዥን ከፈተ። ሦስት ሰዎች በኢትዮጵያ ወቅታቂ ሁኔታ ይከራከራሉ። ትንሽ አዳመጣቸው ፤ እንደሰሞኑ ሁሉ የተከራካሪዎቹ ንግግር ስላናደደው ቴሌቭዥኑን ዘግቶ መተኛት ወሰነ። ቴሌቪዥኑን ቢዘጋውም የክርክራቸው ሀሳብ ግን በህሊናው ሳይዘጋ አብሮት መኝታ ክፍል ሄዶ አላስተኛህ አለው።
“እንዴት ነው የሚያስቡት ? ” ሲል ራሱን ጠየቀ ፤ የሚመልስለት አልነበረም።
ዮናታን ከኢትዮጵያ ከመጣ እንሆ ድፍን አምስት አመት ሆኖታል። ቀዝቀዝ ያለውን የአትላንታ አየር ብቸኝነቱን ሆድ እያባሰበት፤ አንዴ እየተከዘ ሌላም ግዜ እየቀዘመ ንሮ ብሎ በማይቀበለው አኳሀን እየኖረበት ነው።
የክፍሉን ማሞቂያ ከፍቶ ፣ አልጋው ላይ ገደም አለና ፤ ሁሌም እንደሚያደርገው፣ ለስለስ ያለ ሙዚቃውን ከፍቶ ትዝታውን መኮምኮም ጀመረ። ግን ከቴሌቪዥኑ ክርክር ግን ራሱን ማላቀቅ አልቻለም። በተለይ አንደኛው ተከራካሪ የሚያቀርበው የፌደራሊዝም ጉዳት ብግን አድርጎታል።
“እነሱ እዛ ለተናገሩት ፣ እኔ እዚህ የምቃጠለ ምን ቤት ነኝ?” ብሎ ጠየቀና
ራሱን ለማረጋጋት ሞከረ። ሁሌ እንደሚለው ፖለቲካ ቫይረስ ስለሆነ በቀላሉ ተጋብቶበት በቀላሉ ግን አልለቅህ ብሎታል።
***
ሙዚቃው ብዙ ተጫውቷል እሱ ግን በሐሳብ አንዴ ስለ እናቱ አንዴ ስለእናት አገሩ እያፈራረቀ ያስባል። “የእናቴ ውለታ የአገሬ
ትዝታ ባለሁበት ቦታ …” የሚለው ግጥም ጋር ሲደርስ የእናቱ ትዝታ ጠንከር
ስላለበት ፤ ስልኩን አንስቶ ደወለ። ስልኩ ይጠራል ግን የሚያነሳ የለም። ደግሞ ደጋግሞ ደወለ ፤ የሚያነሳ የለም። የዮናታን እናት
ህጋዊ ሥማቸው ወ/ሮ ማንጠግቦሽ አዳፍሪ ይባላሉ። ተጨዋችና ሰው ወዳድ የሆኑ ሰው ናቸው።
ወ/ሮ ማንጠግቦሽ እነ ዮናታንን ለማሳደግ ያላዩት ፍዳ የለም። ኑሮ
በፈጋ ቢሆን ኖሮ፤ የሳቸውን ያህል አሳሩን የበላ ሰው በፍፁም አይገኝም። ከዚህ ሁሉ የንሮ ፍጋት ገንዘብ ባያገኙምበትም
ተግባቢነትና ተጫዋችነት ተክነውበታል።
ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ጋር ለመጫወትና ለመግባባት ሰው ብቻ መሆን በቂ ነው። ብሔር፣ ኅይማኖት፣ ዕድሜና ፆታ አይገዳቸውም። ጫወታቸው
በጣም ደስ ስለሚል ሰው ሁሉ እንዲያጫውቱትና እንዲያስቁት ይፈልጋል። ችግሩ አንዴ ጨዋታ ከጀመሩ፤ ቤታቸው ይረሳሉ። አንዳንድ የሰፈር
ሰው ይህንን ተጫዋችነታቸውን ስለማይወዱት ፤ ማንጠግቦሽ ጨዋታ ስለምታበዛ ነው ትዳሯን በግዜ ፈታ ዘመኗን ሁሉ በብቸኝነት ስትሰቃይ
ነው የኖረችው ሲሉ ያሟቸዋል። በእርግጥ እውነታው እንኳን ያ አልነበረም። ወ/ሮ ማንጠግቦሽ እነ ዮናታን ህፃን እያሉነበር ትዳራቸውን
የፈረሰባቸው። ከዚያን ወዲህ ትዳር ቢፈልጉም ሁለቱን ልጆች እያየ የሚጠጋ ደፋር በመጥፋቱና በኑሮም የሚደግፋቸውም ባለመገኘቱ፤ ሁሉን
እርግፍ አድርገው ትተው፤ አዲስ አበባ ገቡ።
***
ወ/ሮ ማንጠግቦሽ ሁሌም ላገኙት ሰው እንደሚያወሩት ፤ ሰው ዘሩ የሚመዘዘው ከአንድ ሀረግ ነው ይበሉ እንጂ ፤ ሰው ሲጋባ
ዘር ግንዱን አይቶና ትውልዱኑን ቆጥሮ መሆን አለበት ብለው ነው የሚያምኑት። ከዚህም የተነሳ ያችን አዲስ አበባ የምትኖረውና ሜሮን
አባተ የምትባል፣ ትምህርት ቤት ሳለ የተዋወቃትን የዮናታን ሴት ጓደኛ ፣ ለልጃቸው የጋብቻ እኩያው እንዳልሆነች ስለሚሰማቸው ፤
ስለሷ ምንም ነገር እንዲወራላቸው አይፈልጉም። እርሱም ቢሆን ወደፊት ሊያገባት የሚፈልጋት እንደሆነች አይነግራቸውም። ልባቸው ግን
በደንብ አሳምሮ ያውቀዋል ፣ አንድ ቀን ዮናታን ሜሮን አግብቶ በፍቅር አብሯት እንደሚኖር።
ወደ እናቱ ደጋግሞ ደውሎ ሳያነሱት ሲቀሩ ፣ በልቡ የእናቴ ምትክ ወደ ሜሮን ደወለላት። ስልኩ ጠራ እና ብዙም ሳትቆይ አነሳችው።
“እንዴት ነሽ ሜሪ፣ የጠፋሽውስ በሰላም ነው ወይ ?” ብሎ ጠየቃት። ልማድ ሆኖበት እንጂ
የጠፋችውስ ሜሮን አልነበረችም።
“እኔ እንኳን አልጠፋሁም፣ አንተ ነህ እንጂ ፣ ሲደወልልህ የማታነሳ ፥ ኤሜይል ቢላክልህም የማትመልስ።” ምን እያለችው
እንደሆነ ብትክክል ገብቶታል።
ሜሮን ያኔ ድሮ ፣ ዲቪ ደርሶት አሜሪካ ሊሄድ ሲነሳ እንደተነጋገሩት ፤ በቅርቡ አገር ቤት መጥቶ የማያገባት ከሆነ ፤ በመደዋወል
ብቻ የተልዕኮ ፍቅር እንዲኖራት እንደማትፈልግ አውቆ ፤ ውሳኔውን እንዲያሳውቃት ደጋግማ አስታውቃዋለች። ያ የማይሆን ከሆነ ግን
፤ የራሷን መንገድ በግዜ መሄድ እንደምትፈልግ አስጠንቅቃ የፃፈችው ኤሜይል ፅፋለታለች። እርሱ ግን መልስ መስጠት ስላልቻለ እና
ታገሽኝ የሚለው የተለመደው ማረጋጊያው በስልክ መናገር ስለከበደው ነበር ፀጥ ረጭ ብሎ የጠፋው። ዛሬ ግን በአንድ በኩል ፍቅሩ ትዝ
ስላለውና በሌላ በኩል ደግሞ ብርዱ ብቸኝነቱን ስላባባሰበት ፤ የመጣው ይምጣ ብሎ ዛሬ የደወለው። ጭንቅ ጥብብ እያለው ቢደውልም፤
እርሷ ግን ሰላምታ እንኳን በቅጡ ሳትለዋወጥ እንሆ ወደ ጭቅጭቅ ገባች።
ጭቅጭቋን ቀጠለች።
“አሁንም ቢሆን እኔ ለፍቅራችን ስል እስኳሁን ታግሻለሁኝ፤ አንተ ግን ለኔ ስሜት ሆነ ለቤተሰቦቼ ሞራል ደንታ የለህም።
”
እንደለመደው ላማባበልና ለማረጋጋት ሞከረ።
“ስዊት እንደዛ አይደለም። ማመቻቸት ያለብኝ ነገሮች ማመቻቸት ስላልቻልኩኝ እና ነገሮች እንዳሰብኳቸው ስላልሆኑ ነው። እንጂ
እኔ ያንቺን ግዜ ለማቃጠል አስቤ አይደለም።。。。” እያለ እንደተለመደው ባይሳካለትም ሊያረጋጋት መኮረ።
እሷም ብዙ ተናገረችውና ትንሽ ቅር አለው። በንግግሯ ውስጥ የሱን ህሊናቢስነት ላማጉላት የምትጠቀምባቸው ቃላት በእጅጉ አበሳጩት።
ዋጋ ቢስ የሆነ ግንኙነት ሲል ተበሳጨ። ስልኩን ከቅሬታ ጋር ሆነው ተሰነባብተው ዘጉት። እርሷ እንደምታስበው ሳይሆን ፣
ዮናታን የሚኖረው እጅግ ዝቅተኛ የሚባል የንሮ ደረጃ ነው የሞኖረው።
ደስ የሚል ሆነ ተስፋ የሚሰጠ ነገር ሳያጋጥመው ቀኑ መሽቶ ሊታኛ ነው።
***
ከዚያ በፊት ግን ፤ ወንድምዬው ጋ ደውሎ “እማዬ ምን ሆና ነው ስልኩን የማታነሳው ?” ብሎ
መጠየቅ አሳበና ግን ተወው። ምክንያቱም ወንድምዬው አንድ አብሽቅ የሆነ ችግር አለበት። ሲደወልለት አንዳች ችግር ፈጥሮ አውርቶ
ገንዘብ እንዲላክለት ይጠይቃል። ፈጠራው ተነቅቶ ገንዘብ ካልተላከለት ደግሞ ኩርፍያው በጣም አደገኛ ነው።
በዚህ በወጣትነት ዕድሜው ተጧሪ የሆነ አስቸጋሪ ወንድም ስላለው ዮናታን ሁሌም ይበሳጫል። ዮናታንን የሚያስጨንቀው የወንድምየው
ማኩረፍ ሳይሆን ኩርፊያውን ተከትሎ የሚፈጠር የእናታቸው ንዴት ነው።
ወንድምዬው እንደ እኩዮቹ ከቤት ወጣ ብሎ ዞር ዞር የማይለውና ማህበራዊ ህይወቱን የማያዳብረው ሥራ ስለሌኝ ሲሆን ሥራ የማልሰራው
ደግሞ መነሻ ገንዘብ ከአሜሪካ ስላልተላከልኝ ነው ሲል ያስባል። በዚህ ሐሳቡ ዮናታን በጣም ይናደድበታል። እናትዬው ግን ያዝኑለታል።
እርሳቸው ግን ንሮን ለማሸነፍ ያልሰሩት ሥራና ያላዩት ጉድ የለም።
***
ከትምህርት ቤት ጓደኞቹ አብዛኞቹን የረሳቸው ቢሆንም ጌታቸው አለምአየሁ ግን በፍፁም አይረሳውም። ድሮ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች እያሉ ጀምሮ ነበር ጓደኝነታቸው። ጌታቸው አለምአየሁ በጣም አስቂኝ ስለነበረ ፣ ትምህርት ቤት ውስጥ የእርሱን ያህል ተወዳጅ ሰው አልነበረም።
ዮናታንና ጌታቸው
አለምአየሁ ጋር ከተደዋወሉ ቆይተዋል። በሶሺዮሎጂ ማስተርሱን ዲግሪውን አጥንቶ ፣ አዲስ አበባ
ባለው የአውሮፓ ህብረት ፅ/ቤት እንደሚሰራው ያውቃል። ከዚያ ውጪ ግን ከተደዋወሉ ሁለት ዓመት ስላለፋቸው በምን ሁኔታ ላይ እንዳለ
አያውቅም።
***
የዮናታን ችግር ሥራ አለመስራቱ ብቻ አይደለም፤ የፍላጎቶቹ ልክ አለመኖር እንጂ። ዮናታን እንደወንድሙ አይነት አምራች ያልሆኑ
ብዙ ወጪ ስለሚያወጡ ዜጎችን ሲያስብ አገሪቷ ታስጨንቀዋለች። ይባስ ብሎም የአገሪቷ ኢኮኖሚ አደገ ሲባል፤ በምን ስሌት እንደሆነም
ግራ ይገባዋል።
ዛሬ ዛሬ ግን ፣ እንደእናታቸው ያሉ በማቻቻል የሚያምኑ ሰዎች ቁጥር እየቀነሰ በመምጣቱ፤ ሥራፈቶቹ እንደ ድሮ መሆን አልቻሉም።
ለዚህም ሳይሆን አይቀርም ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ በአሪቷ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ያልተጋባ ፋብሪካ የማቃጠል የመሰለ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ
የሚሳተፉት።
የትራስጌ ሰዓቱ ክፉኛ ጮኾ ከእንቅልፉ ስለቀሰቀሰው፤ ከአልጋው እየደበረው ተነሳ። የባጡን የቆጡን እያሰበ እንቅልፍ ሳይወስደው
ረዥም ሰዓት ቆይቶ ፤ ሊነጋጋ ሲል ነበር እንቅልፍ የወሰወድ። ከምኔው እንደነጋም አላወቀውም። ሰዓቱ ማጠሩ እያበሳጨው ፤ ግዜውን
አሳጥሮ በቂ ገንዘብ ወደማያስገኝለት ሥራው ከነፈ።
***
ቢሮ ገብቶ ተንፈስ ሳይል ገና ፤ ያ ሹል አፍንጫ አንቶኒዮ
የተባለ በትውልድ ጣልያናዊ የሆነው አለቅየው፤ ሁሌም እንደሚያደርገው፣ በሩን
ሳያንኳኳ ወደ ዮናታን ቢሮ ዘው ብሎ ገባ። ዮናታን የአንቶኒዮ አኳሀኑ ሲያስበው ግር ይለዋል። የዛሬው ግን ከሁሌም ይለያል።
አንቶኒዮ የያዘውን ሰነድ ወደ ዮናታን ፊት ወዳለው ጠረቤዛ በሀይል ጣለና ቁጣውን አነደደው። ዮናታን ቀና ብሎ በትኩረት
አየው።
አንቶኒዮ የቁጣ ሲቃ እየተናነቀው “ሰርቨሩ ላይ ችግር አለ፣ እነዛ ዲቃሎቹ ዛሬም ሳያገኙን አይቀሩም። እስቲ ሥራኽን በደንብ
ሥራ” አለው እና የዮናታንን መልስ ሳይጠብቅ በመጣበት ፍጥነት ተሽቀንጥሮ ወጣ። ዮናታን ሰርቨሩ ሲመለከተው ፤ ከሚገመተው በላይ እጅግ ተጎድቷል። ዋና ዋና
የመረጃ ቋቶች ተጠቅተዋል። ዮናታን ተናደደ።
ምዕራፍ -
2. የዳይስቶጵያ
አንቶንዮ ዮናታንን የሚያጨናንቅበት ጉዳይ መጣ ተገኘ ማለት ነው። አንቶኒዮ አንድ ስራ አዞ ትንሽ ሲዘገይበት የሚፈጥረው
ጭቅጭቅ ዮናታንን በጣም ያበሳጨዋል። በእርግጥ ያሺያዊያኑም ያበዙታል።
ፋንሲ ቤር የተባለው የራሺያ የመረጃ መረብ ላይ ጥቃት በማድረግ
፤ መንግስታትን፣ የመንግስት መስሪያቤቶችን፣ የግል ኩባንያዎችን፣ ባንኮችን፣ ኢንሹራንሶችን እና ሌሎችን ሁሉ ያጣቃል። የጥቃቱ ኢላማ
አለም-ዓቀፋዊ ስፋት ቢኖረውም ፤ ምዕራቡ አለም ግን ቀዳሚ ተፈላጊ
ወገን ነው።
ዮናታን አሁን በሚሰራበት ተቋም ውስጥ ላለፉት አምስት ዓመታት ሲሰራ ፤ ይህ ፋንሲ ቤሪ የተባለው የመረጃ መረብ አጥቂ ቡድን
ከመቶ በላይ ግዜ ጥቃት አድርሷል።
ሌላው ተመሳሳይ ተልዕኮ ያለውና አፓርትመንት 28 የሚባለውም ቡድን እጅግ የከፉ ጥቃቶች በማድረስ የሚያክላቸው የለም። አፓርትመንት
28 የተባለው የጥቃት ቡድን የሚያክል አደጋ በአለም ላይ አድርሷል የሚባለው በአስጊነቱ በከፍተኛ ደረጃ የሚታየው ጥቁር ነፍስ የሚባለው ቡድን ነው። ይህ ጥቁር ነፍስ የሚባለው ቡድን በተለይ የአሜሪካ ወታደራዊ ተቋማትን
ነጋ ጠባ በማጥቃት ዛሬም ድረስ እጅግ የተፈራ ስምና ዝና አለው።
ዮናታን ጥቁር ነፍስ የሚባለው ቡድን አጥቅቶ አይቶ
አያውቅም። ጥቁር ነፍስ የሚባለው ቡድን ጥቃት ካደረስ ሰነዶቹ
የመገኘትም እድል የላቸውም ይባላል። ዛሬ ግን የደረሰው ጥቃት ከዚሁ ከአደገኛው እንዳይሆን በጣም ፈርቷል። ከሆነ የጠፉ ነገሮችን
መልሶ ማግኘት አይቻልም። ካልተገኘ ደግሞ አንቶኒዮ የዮናታንን የእንጀራ ገመድ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ሊበጥሰው ይችላል።
ዮናታን አሁን ባለችው ንሮው ላይ ምንም አይነት የንሮ ቀውስ እንዲከሰት አይፈልግም። ቢከሰትበት ማንሰራራት አይችልም። አሜሪካ
ከአገሩ ሲወጣ የጠበቃት አይነት አልሆነችለትም። ገቢው አንሶ ንሮውን በበቂ ሁኔታ ለመምራት አላስቻለውም። ወንድሙና እናቱን በየወሩ
የሚልካት ብር ትንሽ ብትሆንም እሱን ለማዳከም በቂ ነች። መጀሪያውኑም እርሱ የተዳከመና መግባት በሌለበት ብድር የተበላሸ ህይወት
ነው ያለውና።
***
የደረሰውን የሳይበር ጥቁቱ ስፋት ቀኑን ሙሉ ጎርጉሮ አጠናና ዝርዝር አዘጋጀ። ይህንን የጥቃት ሪፖርት ማዘጋጀት ፣
በዚህ እርሱ በሚሰራበት ተቋም ውስጥ እጅግ የተለመደ ቀዳሚ ተግባር ነው። ሰርቨሩን ከፍቶ ኤቨንት ሎጎችን ተመለከተ።
በርካታ ነገሮች እንደተከናወነ አወቀ። የሰራተኞቹ የኢሜይል መረጃ ቋቶችን ተመለከተ ፤ አብዛኞቹ ተጠቅተዋል። ድርጅቱ የሚጠቀምባቸው
የተለያዩ አፖችን አንድ በአንድ እየከፈተ አያቸው ፤ በከፋ በሚባል ደረጃ ተጠቅተዋል።
ጥቃቱ የእያንዳንዱን ሰራተኛ ኢሜይል፣ ዋትስአፕ፣ ፌስቡክ፣ ኢስስታግራም እና ዋና
ዋና የመረጃ ቃቶችን አጥቅቷል። በሰርቨሩ ላይ ኧርጀንት ተብለው የመጡ ማሳሰቢያዎችንና እሱ ሳይፈቅድላቸው ሲሰሩ የነበሩ
ራኒግ አፖችን ለማስቆም ፤ ሁሌም እንደሚያደርገው ፣ ሰርቨሩን ለግዜው ብሎክ አደረገው። ያ ሹል አፍንጫ አለቃው መች ፋታ ይሰጥና
፤ ሰራተኞች ስራቸውን መስራት አልቻሉም ብሎ ያምባርቅበታል። የመጣው ይምጣ ማድረግ ያለበትን አደረገ።
መጀመሪያ ኤክስረስ ዋይፋይ ኢንስፔክተር የተባለውን ሶፍትዌር ከፈተና አጠቃላይ ኮኔክሽኖችንና
ሰርቨሩን ፈተሸ። በኮኔክሽኖቹ ላይ የነበሩ እንቅስቃሴዎቹን ሁሉ ተመለከተ። አዳሜ ሁላ ይህንን የተከለከሉ የወሲብ ፊልሞችን የሚያሳዩ
እነ ኤክሰኔክስ የመሳሰሉ አደገኛ ድህረገፆችን ስትከፍት ከርማለች። እነ ጥቁር ነፍስ የሚባለው ቡድን ደግሞ አንዴ ብቻ ይህንን ድህረገፅ ክፈት እንጂ ይጫወቱብሀል።
ኪፓስ ፓስወርድ ሴፍ ሶፍትዌሩን ከፈተው እና የተጠቁ ፓስወርዶችን ዝርዝር አየ። በጣም
ተበሳጨ ያ ጥቁር ነፍስ የሚባለው ቡድን ያላጠቃው ፓስወርድ
የለም የሁሉንም ድምጥማጡን አጥፍቶታል።
ዮናታን ለሁሉም ሰራተኞች በኢሜይል በላከው ማስጠንቀቂያ መሰረት ፋይሎችን መላላክ ያለባቸው በፋይል ዚላ አማካኝነት ነው።
ሆኖም ግን አብዛኞቹ ሰራተኞች ፋይሎችን የሚላላኩት ፋይል ዚላን ሳይጠቀሙ ነው። ያ ማለት እነ ጥቁር ነፍስ የሚባለው ቡድን ፋይሎችን በቀላሉ አነኟቸው ማለት ነው። መጨረሻ ላይ ፍይሉ ተሰርቋል ተብሎ የሚጮኸው
ዮናታን ላይ ነው።
የጥቃቱን ጥልቀት ለመመልከት ሲባል አንዳንድ የሰራተኞች ኮምፕዩተሮችን እዛው ሆኖ በኔትዎርክ መመልከት ጀመረ። ሰቨን ዚፕ
የተባለው ሶፍትዌር ለሁሉም ሰራተኛ የተገጠመለት ትልልቅ ሰነዶችን በቀላሉ እንዲያጭቅበትና ብዙ ሜሞሪ ሳይፈልግ መረጃዎችን መያዝ
እንዲችል ነው። አዳሜ ግን ሙዚቃና የወሲብ ፊልሞችን ነው ያጨቀችበት። አንዳንድ ቢታጨቁ ሊተርፉ ይችሉ የነበሩ ወሳኝ ፋይሎች ተጠቅተዋል።
ያሹል አፍንጫ አለቅየው ሳይመጣና ሳያምባርቅበት መቆየቱ ገረመው። እንዲህ ያለ ጥፋት ደርሶና ይህንን ያህል ሰዓት ሰርቨር
ተቋርጦ መቆሙን መቀበል የሚችልበት ትግስት እንደሌለው በደንብ ያውቀዋል። ብቻ ከሚያንባርቅበት ቪኤምዌር ፕለየርን ከፍቶ ለግዜው
ሰራተኞች ስራቸውን ማስቀጠል እንዳለበት አሰበና ስራውን ሁሉ በቨርችዋል አካውንት ማሰራት ጀመረ። ሲይስተም ኢዝ ባክ ኦንላይን የሚል
መልዕክትም ወደ ሁሉም ኮምፕዩተር አስተላለፈ። አክቲቭ ሰርቨሩን ከፈተና የሰራተኞቹን ኮምፕዩተሮችን እንቅስቃሴ አየ።
***
ተመስጦ በሚሰራበት ቢሮው ውስጥ በድንገት ስልኩ ሲጣራ ትንሽ ደንገጥ አለ። የደዋዩ ቁጥር አስታወሰው ፣ ጌታቸው አለማዮህ
ነበር። ዮናታን ደስ አለ ፤ ጌታቸውን ይወደዋል። ከተደዋወሉ ትንሽ ቆይተዋል።
“ሀሎ ጌች 。。。” አለ ዮናታን ከልቡ
ፈገግ ብሎ ።
“ዮናታን እንደምን
አለህ።” አለ ጌታቸው። ሰላምታ ከተቀያየሩ በኋል ነበር ጌታቸው ወደ ደወለበት ጉዳይ የገባው። የጌታቸው አባት አቶ አለማዮህ በመታመማቸው
የታዘዘላቸው መድሀኒት አዲስ አበባ ውስጥ ፈልጎ በማጣቱ ፤ ዮናታን ያንን መድሀኒት ገዝቶ እንዲልክለት ጠየቀው።
“ምንም ችግር የለም
ፕሪስክሪብሽኑን ፎቶ በቫይበር አሁኑኑ ላክልኝ። ዛሬ ገዝቼ በዲኤች ኤል በሦስት ቀናት ውስጥ ይደርስሀል።” አለ ዮናታን በአቶ ጌታቸው
የደረሰባቸውን የጤና ቀውስ ከልቡ እያሳዘነው። ጌታቸውም ላገኘው ምላሽ ከልቡ አመስግኖ ተሰነባብቱ።
***
ምን እንዳነሳሳው ሳያውቀው ያቺ ሙና የምትባል ኢትዮጵያዊት የምትጠቀምበትን ኮምፕዩተር አየውና ዝም ብሎ ከፋፈተው። ሙና
ደስ የሚል ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የተላበሰች ቆንጆ ሴት ናት ብሎ ስለሚያምን እንዲሁ ይወዳታል ያከብራታል። የሰይጣን ነገር ሆኖ ግን
አንድም ቀን በህልሙም በዉኑም ለፍቅር ሆነ ለጓደኝነት አሊያም ለግዚያዊ ግንኙነት ተመኝቷት አያውቅም።
ሁሌም እንደተለመደው እንዲህ ያለ አደጋ ሲደርስ ሰራተኞች ሁሉ የጠፋባቸው አሊያም የተጎዳባቸው መረጃ ካለ ሪፖርት ያደርጋሉ።
የሪፖርቱ ግልባጭ የሚላከው ወደ ዮናታን ነው። የሁሉም ሰው ሪፖርት አንድ በአንድ ከተመለከተ በኋላም ሊስተካከል የሚችሉትን ያስተካክላል
የጠፉትን ደግሞ ከገቡበት ገብቶ ሪከቨር ያደርጋል።
***
ዮናታን እንዲህ ያለ ጥቃት ሲደርስ በርካታ የጠፉ ፋይሎችን ሪከቨር ማድረጊያ ሶፍትዌሮች የሚጠቀም ሲሆን ፤ ዛሬ ግን ሥራው
ስለበዛ ሪከቫ ዋንን መጠቀም ወሰነና ከፈተው። ሪከቫ ዋንን ፈጣንና ምርጥ የጠፉ ፋይሎችን ሪከቨር
ማድረጊያ ሶፍትዌር ነው። የሪከቫ ዋንን ዋናው ችግር የተገኙ ፋይሎችን ወደየነበሩበት ቦታ መመለሱ
ላይ እጅግ ይዘገያል። ፑራን ፋይል ሪከቨሪ የሚባለው ደግሞ
ሲፈልግ ይዘገያልም አንዳንዶቹንም አያገኛቸውም እንጂ ለመመለስ እንኳን ብዙም ችግር የለበትም።
በእርግጥ ሰርቨራቸው ያለው ፕሮሰስ የማድረግ አቅም ከፍተኛ ነው። አንድ ፈጣን የሚባል ላፕቶፕ ሳያቋርጥ ለሰላሳ ዓመት ቢሰራ
የማይጨርሰውን ስሌት በአንድ ሰዓት የሚሰራ ነው። እንዲ ያሉ ሰርቨር ያላቸው ኩባንያዎች በጣም ጥቂት ናቸው።
ሪከቫ ዋንን ፋይሎቹን ሁሉ ከገቡበት ገብቶ መዘርገፍ
ጀመረ። እጅግ ብዙ የሆነ የፋይል ብዛት ተገኘ። ሪከቫ ዋንን ፋይሎችን
እና ፎልደሮችን በስርዓት በስርዓቱ እየደረደረ ይከንፋል። ዮናታን ትንሽ ተንፈስ አለ።
***
የተከበራችሁ ሰራተኞቻችን ፋይሎቹ ሪከቨር የማድረጉ ስራ እየተጠናቀቀ ሲሆን የጠፉ ፋይሎች ሁሉም ሪከቨር የማድረጉ ሥራ እየተከናወነ
ነው። ይህም ከሁለት ሰዓታት በላይ እንደማይፈጅብን ተስፋ አደርጋለሁ። እስከዚያው ግን በትግስት እንድትጠባበቁ እጠይቃለሁ የሚል
መልዕክት ለሁሉም ሰራተኞች ተላለፈ።
ሰርቨሩና ኮምፕዩተሮቹ አደጋው ከመድረሱ በፊት ከነበረው መረጃ ጋር በማነፃፀር የጠፉትን ሪከቨር ከተደረጉት ጋር የሚያነፃፀረው
ዲፕ ስካን ኮምፔር ሶሉሽን የሚባለውን ሶፍትዌር ከፈተና ማጣራት
ጀመረ። በርካታ ሚሊዮን ፋይሎችን በየሰኮንዱ እያጣራ በይዘት አሊያም በስያሜ ልዩነት ያላቸውን ፋይሎች በየኮምፕዩተሩ ስምና ፎልደር
አድራሻ እያደራጀ ማሳየት ጀመረ።
***
የኢትዮጵያዊቷ ሙና ኮምፑዩተር ላይ ልዩነት አላቸው ብሎ ዲፕ
ስካን ኮምፔር ሶሉሽን ከለያቸው ፋይል ስሞች አንዱ ንፋሱ የሚል ስለነበር የዮናታን ቀልብ በድንገት እዛው ንፋሱ የሚለው የፋይል
ስም ላይ አረፈ። ዝም ብሎ ሳበውና ፋይሉን ሙናን በሚያይበት አክብሮት ማየት ጀምሮ በተናጠል በጥንቃቄ ከጠፋበት ገብቶ ሪከቨር ሊያደርገው
ወሰነ።
“ይሄኔ ፋይሉ ሙና በትርፍ ሰዓቷ የፃፈችው የፍቅር የግጥም መድብል ይሆናል፥ ማን ያቃል። አሊያም የግል ህይወቷ በየቀኑ
የምትፅፍበት ዲያሪዋም ሊሆን ይችላል። እንደዚያ እንኳን ባይሆን ጥሩ ነው። ምክንያቱም ሚስጥሯ ሳየው፣ አንዳች ለሷ ያለውን ክብር
የሚቀንስበት ነገር ላገኝ እችላለሁና። ግንኮ የሷን ፋይል ለምን ከፍቼ አየዋለሁ። ይህማ ስለወቅኳት መብቷን ጣስኩት ማለት ነው።
አይ አይ ሌላውን አላይም ፤ ንፋሱ የሚለውን ግን በቃ እፈልገዋለሁ፣ አግኝቼ አየዋለሁ።” ብሎ ብቻውን ሲቀበጣጥር ቆየና፤ ዲፕ ስካን ኮምፔር ሶሉሽን ሪከቨር አድርጎ ሲጨርስ ልዩነት ላሳዩ
እንደነ ንፋሱ የመሳሰሉ ፋይሎችን ዳግም እንዲፈልግ ጎ ኤንድ ሪከቨር የሚለውን ተጫነ።
በርካታ ፋይሎች በቀድሞ ትክክለኛ ይዘታቸው መገኘት ጀመሩ። ሪከቨር የተደረጉ ፋይሎች ውስጥ ንፋሱ የሚለው ፋይል መገኘቱን
ሲያውቅ ደስ አለው።
“ሶሪ ሙናዬ” አለ ጮኽ ብሎ። ደግነቱ እርሱ ቢሮ ውስጥ ማንም
የለም።
ፋይሉን ከፈተው ፤ አንዳች ያልጠበቀው ሰይጣናዊ የሚመስል መንፈስ ከሙና ወደ እርሱ የመጣ መሰለው። በጣም የሚደብር ፋይል
ሆኖ አገኘው። ፋይሉ የፍቅር ግጥም፣ የግል ዲያሪ አሊያም ለፍቅረኛ የተፃፈ ደብዳቤ ሳይሆን ፤ ኢትዮጵያን ሶሪያ ለማድረግ የተዘጋጀ
ዝርዝር ዕቅድ ነው።
“ማመን የማይቻል ጉድ。。。” አለ ጭንቅላቱን በአግራሞት
እያወዛወዘ። ዋችሚ የሚባለውን ሶፍት ዌር ከፈተና ፋይሉን እዛው ዝርዝር ውስጥ አስገባው።
***
“ሀሎ ሜሪ ስዊት እንዴት ነሽ?” አለ ዮናታን ሜሮን በመደወሏ ደስ እያለው።
“ሰላም ነኝ ”
“አቃለሁ አንተን ለመበደል አይደለም፤ ግን ማሰብ ያለብህ እኔ ሴት ነኝ። እድሜዬ እየሄደ ነው። ቤተሰቦቼም መግቢያና መውጫ
ስላሳጡኝ 。。。” ብላ ንግግሯን ሳትጨረስ
ዮናታን አቋረጣት።
“እኮ ሜሪዬ አወራን
አይደል እንዴ ፣ ለምንድነው ጉዳዩን ሳምንት ሳይሆነው ዳግም የምታነሺው?!”
ይህን ሲል በሱ ቤት ሊነገረው የታሰበውን
መርዶ በፍፁም የሚጠረጥረው ዓይነት አይደለም።
“ዮኒዬ አሁን የደወልኩልህ
ወሬውን ከሌላ ከምትሰማ እኔው ልንገርህ ብዬ ነው። ላገባ ነው። ” ዮናታን ላገባ ነው የሚለውን ሐረግ ከስልኩ መድፍ ፈንድቶ አናቱን የበረቀሰው ነበር የመሰለው። ከዚያ ቀጥሎ ያሉትን ንግግሮች መረዳት
አልቻለም። የማሳመኛ ምክያቶች ሜሮን ስትደረድር እንደነበረች ግን ትንሽ ትንሽ ሰምቷል።
ምዕራፍ 3. ዙሪያ መለስ
እንቅልፍ ሳይወስደው አልጋው ላይ ይገላበጣል። ያለ እንቅልፍ አልጋ ላይ እንደመሆን አስጠሊታ ነገር የለም። ሙዚቃ ከፈተ
፤ ግን ምንም አላስደስት አለው። የቶኒ ብራክስተን ዘፈኖችን በጣም ነበር የሚወዳቸው። ዛሬ ግን ከእንቅልፍ ማጣቱ ጋር ተደራርቦ
ሙዚቃው ኳኳታ ሆኖ ነው የሚሰማው።
በሐሳብ አንዴ አገር ቤት አንዴ እናቱን፣ ከዚያም ፍቅረኛው እያፈራረቀ ሲያስብ ቆየና በመሀሉ ሙናና ያ ንፋሱ የተባለው ሰነዷ
ትዝ አለው። ግርምቱ ለራሱ ፈገግ አስባለው።
ሙናን ዝም ብሎ በአይነ ህሊናው አጤናት። በነገሮች ላይ እጅግ ቆጠብ ያለችና ለኢትዮጵያና ለኢትዮጵያዊያን ልዩ ፍቅር ያላት
እንደሆነ ነው የሚያውቀው። ወንድ ሆነ ሴት ጓደኛ የማታበዛ፣ ብዙም እዩኝ እዩኛ የማትልና ረጋ ያለች ተወዳጅ ሴት መሆናን ብቻ ታየው።
በበዓላት ግዜ እነዛ የሚያማምሩ የሐበሻ ልብሶቿን ለብሳ ከሐበሻ ሴቶች ጋር ረጋ ብላ ስትጫወት በተደጋጋሚ አይቷት እንደነበረ አሰላሰለ።
ከዚያ ውጪ በምንም መንገድ እሷን ከሴራ ጋር አያይዞ ማየት አልቻለም።
ሜሮን ፍቅረኛው ስልክ ላይ ስላበሳጨችው ቀልቡ ወደ ሙና የተሳበ መሰለውና ስሜቱን ጠላው። ወዲያውኑ ለራሱ ነገረው።
“ሜሪ የድሮ ፍቅረኛዬ፣ የምወዳትና በምንም የማልተካት። ነገሮችን በቅርቡ አስተካክዬ፣ አግብቻት መኖር የምፈልግ ውድ ፍቅረኛዬን
በማንም አልተካትም። በተለይ ደግሞ ሙና በመሰለች ባንዳ።” ሳያስበው ባንዳ ብሎ ሙናን መፈረጁን ገረመውና ፤ ፍረጃው ምክንያታዊ
አይደለም ብሎ አሰበ። የባጡን የቆጡን ሲያወጣና ሲያወርድ በመሀሉ እንቅልፍ ወሰደው።
***
መኪናውን አቁሞ ዞር ሲል ኢትዮጵያዊቷ ሙናን እስከነ ሙሉ ሞገሷ መኪናዋን አቁማ ስትወጣ አያት። ቆሞ ጠበቃትና ሰላምታ ተለዋወጡ።
ተያይዘው ቢሮ ድረስ እያወሩ ሄዱ። ስለሥራ ፣ ስለ ቤተሰብ እና ስለመሳሰሉት ቀላል ጉዳዮች አወሩ ፤ አብሯት ለመሆን የማትከብድ
ፍቅር የሆነች ሴት ሆና አገኛት። ሲሰናበታት ያሳየችው ፈገግታና ቀረቤታ
እባክህ ቅረበኝ ብላ የምትማፀነው ያለች መሰለው። ችምችም ያሉ ጥርሶቿ ፈገግ ስትልባቸው ምትሀታዊ ሀይላቸው አንዳች ዓለምን ሁሉ
ትታችሁ ፣ ቅረቡኝ ቅረቡኝ የሚል ብርቱ መልዕክት አላቸው።
ሙናን ከመቸውም ግዜ በላይ ሊቀርባት ወሰነ። ግን ሴራውስ ? ወገኖቹስ ? አገሩስ ? ፓቶጵያስ ፤ ብቸኛዋ የሰው
ልጆች የወደፊት ተስፋቸውስ ?
ከመቼውም በላይ ቀረባት፤ እሷም ቀረበችው። ጋበዛት ፣ እርሷም ጋበዘችው። ቤቱ ጠራት ፣ እርሷም ቤቷ ጠራችው። በጥሩ ቤተሰብ
ያደገችና ስርዓት ያላት ሴት ሆና አገኛት። ቤቷ የሄደ ግዜ የፎቶ አልበሟን ጋብዛው አየቶታል።
በሻይ ሰዓት አብረው ሻይ ሊጠጡ ተደዋወሉና ተገናኙ። ዳርዳር እያለም ስለ ታሪክ ስለ እምነት የሳሰሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ
ያላት አቋም ለማጤን ሞከረ ፤ አንዳች ከገመታት ወጥቶ ሰነዱ የእርሷ ነው የሚያስብል ነገር አላየባትም። ቀልድ እና ጨዋታ በጣም
ታውቃለች። ወሬዋ ሁሉ በጣም ደስ ይላል። የሻይ ሰዓቱ ሲያልቅ ፤ ተሰነባብተው ወደየ ቤሯቸው ገቡ።
ቢሮ ገብቶ የጠፉና ያልተገኙ ሰነዶችን እያፈላለግ እያለ ንፋሱ የሚባለው ሰነድ መከፈቱ ዋችሚ የሚባለው ሶፍትዌር ጠቆመው።
ሙና እንደገባች የከፈተችው ይህን ፋይል ነው።
***
“ለምን በደንብ አልሰልላትም፣ ያኔ ይወጣ የለ ጉዱ…” ብሎ አሰበና ፤ በጥልቀት ሊሰልላት
ወሰነ።
ሰርቨሩን ከፍቶ፣ ንፋሱ የሚባለውን ፋይል ላለፉት አንድ አመት በየቀኑ ለሁለት ሰዓታት ያኽል እየከፈተች ኢዲት ስታደርገው
እንደነበር አየ።
በኮምፕዩተሯ ላይ በሥራ ቦታዋ ሆና የምታወራ ወሬና የስልክ ድምፃን ጨምሮ መስማት የሚያስችለውን ትሬስ ኤንድ
ትራክ ሶፍትዌር ጫነባትና መከታተል ጀመረ። ለአንድ ሳምንት ያለማቋረጥ ቀኑን ሙሉ እየቀዳ ፣ ሌሊቱን ሲያዳምጥ እያደረ
ሰለላት። ሁሉን አወቀው። ያ ከበስተኋላዋ ያለውን ድርጅት ማን እንደሆነ ማወቅ ግን አልቻለም።
ኢትዮጵያዊቷ ሙና በእናት አገሯ ላይ እንዲህ ያለ ሴራ እያሴረች ነች ብሎ ማሰብ እጅግ ከበደው። ሙናን ደጋግሞ ተመለከታት።
ዋናው የሙና እና ከበስተጀርባዋ ያለው ሀይል አላማ አንድና አንድ እንደሆነ አወቀ። ፓቶጵያ - ብቸኛዋን የሰው ልጆች የወደፊት ተስፋን
ከገፅ ምድር ማጥፋት።
***
ፓቶጵያን ይበልጥ ለመረዳት ቅድሚያ ሁለት ነገሮችን ማጤን ነበረበት። አንደኛው ኢትዮጵያን ከቅድመ ሰው እሰከ ዘመናዊው ሰው
መረዳት እና ፤ ሁለተኛው ደግሞ አቶጵያ - የመጨረሻው የሰው ልጆች አንድነት። ወደፊት የሰዎች ዛሬ ያሉባቸውን እጅግ በርካታ ችግሮችን፣
ሁሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ፈትተው፣ ዜግነትና ጦርነት አልባ የሆነችዋን ምድር ትፈጠራለች። ያኔ ያችን ዓለም አቶጵያ ብለው ይጠሯታል።
የአቶጵያ ዋና ከተማና የመንግስቷም መቀመጫ ፤ የሰው ልጆች መገኛ በሆነችዋ በኢትዮጵያ ይሆናል። የሰው ልጆች ከኢትዮጵያ
ወደ አቶጵያ ለመሸጋገር ግን ኢትዮጵያዊያን ፓቶጵያን መመስረት አለባቸው። ይህ እንዳይሆን የሚታገሉ አካላት እጅግ ብዙ ናቸው።
ዮናታን አቶጵያ ናፈቀችው። ዓለም ሁሉ ግን የተሰለፈው ፀረ ፓቶጵያ ነው። ድፍን አሜሪካና አውረፓ የሚገኙ ድርጅቶች፣ የምርምር
ተቋማት፣ መንግስታት ሁሉ ፓቶጵያን አይፈልጓትም። የአውረፓ ህብረት የአቶጵያ መቀመጫ ሊሆን የሚችል ሀገር ሆነ ከተማ እንደማይኖር
ይታወቃል ፤ ምክንያቱም ብርቱ ታሪካዊ መነሻ ያስፈልጋልና።
የአሜሪካ ሳይንቲስቶችና የሰው ልጅ አመጣጥ አጥኚዎች ፣ የሰው ልጅ የተገኘው በኢትዮጵያ ነው ፣ ከምድራዊነት ወደ ፕላኔታሪያዊነት
የሚያድገውም በዚያው በኢትዮጵያ መሆን አለበት። ይህ ግን ለአሜሪካዊያኑ ትልቅ ሽንፈት ነው። ስለዚህ ኢትዮጵያ ወደ ፓቶጵያ ሳታድግ
እስከነታሪኳ ብትጠፋ አዲስ የዓለም ታሪክ ቢፃፍ የአቶጵያ ዋና ከተማ ፣ በዛሬዋ በዓለም ንግድ ከተማዋ በኒውዮርክ መሆን ይችላል።
ቻይናዊያኑ ዓለምን ሁሉ ወደ ቤጂንግ የሚያገናይ መንገድ ሲልከን ቤልት በሚባለው ፕሮጀክት ሥም መስራት ከጀመሩ እንሆ ዓመታት
አስቆጥረዋል። ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ የአቶጵያ ዋና ከተማ ቤጂንግ የተሻለ አይኖርም ፤ ከተገኘ ግን ኢትዮጵያ ናት። ስለዚህም ቻይና
ኢትዮጵያ ወደ ፓቶጵያ አድጋ የአቶጵያ ወዲና መሆን የለባትም ባላ ታምናለች።
አረቦቹ እና ህንዶቹ ፓቶጵያ መጥፋት እንዳለባት የሚያሳምናቸው ሚሊዮን ታሪካዊና ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች አሏቸው። ታላቁ ነብያችን
ሆኑ መሲሁ ለኢትዮጵያ የነበራቸው ፍቅር እንኳንስ የሰው ልጆች መናፍስትንም በማናደዱ ዓለም ሁሉ ፀረ ፓቶጵያ ይቆማል።
ዮናታን ብዙ መረመረ ፣ አጠና ፤ ሐቁን ሲያውቀው ዓለም ሁሉ አስፈራው።
***
ሙናን ለመሰለል ሪኮርድ ያደረገውን ይዞ ቤቱ ሄደ። ሲያዳምጣው አደረ። ከሙና ጋር የሚደዋወሉ ሰዎች ብዛት ገረመው። አብዛኞቹ
የሚያወሩት በአማርኛ ሲሆን በትውልድም ኢትዮጵያዊያን ነበሩ።
ከሚያወሩትና ከሚቀጣጠሩበት ቦታ እንደተረዳው ኦርቶዶክሶች፣ ቤንጤዎችና ሙስሊሞች እንደሆኑም ተገነዘበ። ማመን አዳገተው።
ይህ ሁሉ ሐበሻ ፓቶጵያ እንዳትፈጠር ኢትዮጵያን ለማጥፋት የሚተጋ መሆኑ ለማመን አዳጋች ሆነበት።
ዮናታን አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት አሰበ። ንፋሱ የተሰኘው ሰነድ ስትራቴጂካዊ እቅድ የያዘ ይሁን እንጂ ሌሎቹ ከሙና
ጋር የሚደዋወሉትም ሰዎች የየራሳቸው ሰነድ ሊኖራቸው እንደሚችል ገመተ። የሙና ኢሜይሎች ሁሉ ሀክ ማድረግና መበርበር።
በስልክ ሲቀጣጠሩ በሰማው መሰረት እሁድ ጠዋት ላይ ቤተክርስትያን ሄደ። አስቀድሶ ሲወጣ በርካታ ወንድና ሴት ሐበሾችን ከሙና
ጋር አገኘ። አለባበሳቸው ፀአዳና ንፁሕ ቢሆንም አብዛኞቹ ግን በእናት ሀገራቸው ላይ የሚያደቡ ተኩላ ሆነው ታዩት። ፍረጃው ኢምክንያታዊ
እንደሆነ ቢገባውም ከዚህ የተሻለ እነዚህን የሚገልፅበት መንገድ አጣ።
ሰላምታ ሰጣቸው ፤ እነሱም አፀፋውን መለሱለት። አንዱ ከማኸላቸው ከእነርሱ ጋር ሻይ ቡና እንዲል ጋበዘው። እነዚህን ቶክላዎች
ቀርቦ ለማወቅ ጥሩ መንገድ የተገኘ ስለመሰለው ሳያቅማማ አብሯቸው ሆነ።
***
ወሪያቸው ሁሉ እጅግ የተጠና የሚመስል ነው። ወሬው በአብዛኛው አንድ እጅግ መንፈሳዊና አገር ወዳድ ዜጋ የሚያወራው አይነት
ነበር። ሁሉም ተመሳሳይነት ቢኖረውም ፤ ብዙ ነው የሚያወሩት።
“የሰሞኑ ያአገራችን ሁኔታ እጅግ ያስፈራል ፣ አንዱ በአንዱ ላይ ያለው ጥላቻ ቅጥ እያጣ ሄዷል። እንዲያውም የእርስ በርስ
ጦርነቱ አይቀሬ ነው እየተባለ ነው።” አለ አንዱ ዲያቆን እያሉ የሚጠሩት መልከ መልካሙ ወጣት መሳይ ጎልማሳ ሰው።
“የእርስ በርስ ጦርነቱ ከተነሳ ማቆሚያ አይኖረውም። ብንችል ግን እኛ ሁላችን ይህንን ለማስቆም አንዳች ነገር ማድረግ ይጣበቅብናል።
ፍጥነትም ሊኖረን ይገባል…” አለች ሙና። ያኔ ዮናታን ወሬውን መቋቋም አቃተው።
“እባቦች፣ በእናት አገራችሁ ላይ፣ በእሁድ ቀን በደጀ ሰላም ተቀምጣችሁ እንዲህ የምታሴሩ …” ብሉ መናገር አሰበና ግን ለፓቶጵያ ፍቅር
ሲል ዝም አለ።
“እስቲ እንበርታ ፣ አንዳች ነገር እናድርግ። በሉ ውዕቱ በሰላም ” አለ ዲያቆን እያሉ የሚጠሩት መልከ መልካሙ ወጣት መሳይ
ጎልማሳው ሰው።
ሁሉም መንፈሳዊ ሰዎች እንደሚያደርጉት በመልካም አሳሳም ተሳስመው ተለያዩ።
አስተያየቶች